ቦይንግ ከኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋ በኋላ 40 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከስሯል

ግዙፉ የዓለማችን የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የአውሮፕላን አደጋን ተከትሎ 40 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መክሰሩ ተነገረ።

በስድስት ወራት ውስጥ ቦይንግ 737 ማክስ 8 የተሰኘው አውሮፕላኑ በአንዶንዥያ እና ኢትዮጵያ በሚመሳሰል ምክንያት መከስከሱን ተከትሎ ኩባንያው እሳት ላይ ተጥዷል።

ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ሁሉም ሀገራት ይህን አውሮፕላን ከበረራ አስወጥተዋል።

ይህም በመሆኑ የኩባንያው የአክሲዮን ድርሻ በ18 በመቶ ቀንሶ 40 ቢሊየን ዶላር ክስረት ገጥሞታል ብሏል ሲ ኤን ኤን በዘገባው።

Please follow and like us:

Related posts

Leave a Comment