ኤርትራ “ሱዳን፣ ኳታርና ቱርክ ክፉ አስበው እያሴሩብኝ ነው” ስትል ከሰሰች

የኤርትራ መንግስት ዛሬ ባወጣው የቱርክ መንግስት በተለይም ገዢው ፓርቲ ኤ ኬ ፒ አልፎ አልፎ በኤርትራ ላይ የሚፈፅመው ደባ አሁን ላይ ግልፅ እየወጣ ነው ብሏል የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ።

ይህ ከንቱ ሙከራም በኳታር የገንዘብ ድጋፍ እና በሱዳን መንግሰት ትብብር እየተከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተለይም የሱዳን መንግስት ለዚህ ድርጊት የሀገሪቱን ግዛት ፈቅዷልም ነው ያለው።

የድርጊቱ ዋና ዓላማም በቅርቡ እየተሻሻለ የመጣውን የኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነትና ሰላማቸውን ማወክም እንደሆነ ገልጿል።

የኤርትራ መንግስት በመግለጫው ለዚህ ድርጊት ቱርክ በቅርቡ በኤርትራ ኡላማ ሊግ ስም የኤርትራ ሙስሊም ሊግ ቢሮን መክፈቷን አግባብ አለመሆኑን ነው ያነሳው።

ኤርትራ ሀገራቱ ይህን በክፋት ድርጊታቸው ቢገፉን እኩይ ምግባራቸው ግን ፍሬ አያፈራም ብሏል።

Please follow and like us:

Related posts

Leave a Comment